ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

ሰሜን ኮሪያ ሁለት የባልሰቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር ማስወንጨፏ ተነግሯል፡፡

ይህም ሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያደረገቻችውን የሚሳኤል ሙከራዎች  አምስት አድርሶታል፡፡

ከደቡብ ሃምግዮንግ ግዛት ሃምሁን ከተማ እንደተተኮሱ የተነገረላቸው  ሁለቱ ሚሳኤሎች በጃፓን ባህር የኮሪያ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ማረፋቸው ተነግሯል፡፡

የባሊስቲክ ሚሳኤሎቹ  የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊዎች ሊሆኑ እንደሚችልም የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያ ሰላማዊ መልዕክት እንደደረሳቸው ከገለጹ በኋላ ሰሜን ኮሪያ ወደ ባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ተመልሳ ገብጻለች፡፡

የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው የደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደረዊ ልምምድ እንዳልተዋጠላቸው ገልጸው እንደነበረም ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡