ህንድ ግዛቶቿን ወደ ነበረበት ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ

ህንድ ግዛቶቿን በተመለከተ ወደ ነበረበት ታሪክ ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ጉዳይ በተለየ መልኩ የሚታይ እና ለሀገራቸው የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የካሽሚር ግዛት ህንድ በኢንግለዝ ቅኝ ግዛት ከመገዛቷ በፊት የህንድ እንደነበረች የሚነገር ሲሆን፣ ሀገሪቱ በቅኝ ግዛት ስር መውደቋን ተከትሎ በቀጠናው ላይ መበጣጠስ ሲመጣ ጊዛቲቱ በተለያዩ ሀገራት ማለትም በፓኪስታን እና በህንድ ስር ተከፋፍላለች፡፡

ታዲያ ህንድ የካሽሚርን ግዛት በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያቶች የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ብትሆንም በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት አልቻለችም፡፡ በዚህ ጉዳይ የካሽሚር ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ ህንድ መልስ ለመመለስ መጣር ብቻ ሳይሆን ከጎሮቤቷ ፓኪስታን ጋርም እሰጣ ገባ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል፡፡

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግልጫ ሀገራቸው ህንድ ወደ ነበረችበት የቀድሞ ታሪክ መመለስ አለባት፤ ለዚህም መንግስታቸው በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ መናገራቸው ተገልጸዋል፡፡

ህንድ ከኢንግሊዝ ነፃ የወጣችብትን 70ኛ እና ከፓኪስታን የተለያየችበትን የነፃነት ዓመት ስታከብር ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ግዛት በህንድ ሉዓላዊነት እና ለእድገቷ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ነች፤ ስለዚህም ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ያለማመንታት ካሽሚር ወደ ቀድሞ ማንነቷ ትመለሳለች ማለታቸዉን የወጡት ዘገባዎች አስነብበዋል፡፡

ናሬንደራ ሞዲ ሀገራቸው ሁሉን በልኩ ሊስተካክል የሚያስችል ህገ መንግስት እንዳላት ተናግረው ነገሮች ሁሉ በዛ ይስተካከላል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ከህንድ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ያለችው ፓኪስታን ህንድ ለመውሰድ ለምተዘጋጀው እርምጃ አፀፋዊ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብላለች፡፡

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ ለመፋለም ተዘጋጅተናል ማለታቸዉን ቢቢሲ አስንበቧል፡፡

የዓለም ሁሉ ዓይን በካሽሚር እና በፓኪስታን ላይ ነው፡፡ ህንድ ስለምታደርገው ነገር ሃይ ባይ ባጣችበት ውቅት ላይ እኛ ለእርምጃ ተዘጋጅተናል፡፡ ነገር ግን ለሚሆነው ሁሉ ኃላፊነቱን የዓለም ማህበረስብ ራሱ ይወስዳል ብለዋል ጠቅላይ መኒስትር ኢምራን ከሃን፡፡ በዚህ መልስ ግን ናሬንድራ ሞዲ ያሉት ነገር የለም ነው የተባው፡፡

(ምንጭ፡-አልጀዚራ፣ ቢቢሲ እና ኢንዲያን ቱደይ)