በ2045 ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት 100ኛ ዓመት በሚከበርበት እ.አ.አ 2045 ላይ ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሙን ይህንን ያሉት ኮሪያ እ.አ.አ ከ1910-1945 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከነበረችበት የጃፓን አገዛዝ ነፃ የወጣችበትን 74ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ነው።

ሙን በሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን እና በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል ከኒዩክሌር ነፃ መሆን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ አራተኛ ውይይት እንዲካሔድ እየገፋፉ ይገኛሉ።

ከኒዩክሌር ነፃ መሆን እና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማድረግ በሰላጤው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል መሠረት ለመጣል ወሳኝ ነው ብለዋል።

ሙን፣ ሴኡል እና ፒዮንግያንግ እ.አ.አ በ2032 በጋራ ኦሎምፒክን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ እና እ.አ.አ በ2045 የሁለቱን ኮሪያዎች ውሕደት እውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም፣ “ለራሷ፣ ለምሥራቅ እስያ እና ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና የምታመጣ አዲሲቷን የኮሪያ ሰላጤ እየጠበቅን ነው” በማለት ሐሳባቸውን ደምድመዋል። (ምንጭ:-ዘጋርዲያን)