የአልሻባብ የሽብር ቡድን ቃል አቀባይ ለሶማሊያ መንግሥት እጁን መሥጠቱን አስታወቀ
በሶማሊያ በስፋት እንደሚንቀሳቀስ የሚታወቀው የአልሸባብ የሽብር ቡድን ከፍተኛ አዛዥ እና ቃል አቀባይ የሆነው ሙክታር ሮቦው ወይም በታጣቂው ቡድን አል መንሱር ተብሎ የሚጠራው ግለሰብ ለሶማሊያ መንግስት እጁን ሰጥቷል፡፡
አል ሸባብ የተሰኘው የሽብር ቡድን በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃቶችን እንዲሁም ከተለያዩ አለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር በመሆን ብዙ ቦታዎች ላይ የብዙ ሺዎችን ህይወት ሲቀጥፍ የቆየው እና ከቅርብ ጊዜ በኋላ ደግሞ ሶማሊያን ግብ ያደረጉ ብዙ ሽብሮችን እንዲፈጥር ይታወቃል ፡፡
ሙክታር ሮቦው ከአል ቃኢዳ የሽብር ቡድን ጋር በሰፊው ግንኙነት እንዳለው የሚታወቀው ይህ የሽብር ቡድን አባል እና ለሚፈጽማቸው የሽብር ጥቃቶችም ከአሜሪካ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት የሚታሰበው ግለሰብ በአንድ ወቅት የሽብር ቡድኑ ምክትል መሪ እና መረጃ አቀባይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከአራት አመታት በፊት የአልሸባብ መሪ የነበረው አህመድ አብዲ ጎዳን የአሜሪካ ኃይል የአየር ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት በጥቃቱ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ የራሱን ደህንነትም ለመጠበቅ ያስችለው ዘንድ በትውልድ ሀገሩ ሶማሊያ የራሱን ደጋፊዎች እና ሌሎችንም በማሰባሰብ በሶማሊያ ደቡብ ምዕራባዊ በኩል የምትገኘውን ባኩል ግዛት ውስጥ በመስፈር የተለያዩ ጥቃቶችን ሲዘነዝር ቢቆይም የግዛቱን መቆጣጠር ግን በይፋ ሳይናገር ቆይቷል፡፡
የባኩል ከተማ ዋና ግዛት የሆነችው የሁዱር ግዛት የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር ሙሀመድ ሙአሊም ለጋዜጠኞች እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ሙክታር ሮቦው ከሽብር ቡድኑ በመነጠል ከመንግስት ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገርም እነሱ ጋር እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ማንነቱ ያልተጠቀሰ የደህንነት መረጃ ምንጭ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንዳለው ሮቦው እጁን ለመንግስት ሊሰጥ የቻለው በባለፈው ሳምንት ያልታወቁ የታጣቂዎች ቡድን እሱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ከሞከሩበት በኋላ ነው ብሏል፡፡
እጅ መሥጠቱን ተከትሎ አሜሪካ እሱን እና ሌሎች የሽብር ቡድን መሪዎችን ለሚያድኑ ግለሰቦች ሽልማት ለመስጠት አውጥታው ከነበረው የተፈላጊዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሙ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ መሪ ወደ መንግስት መቀላቀሉ በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ሥር 22 ሺ ወታደሮችን የያዘው ተልዕኮን እንዲሁም የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሀገራት ለሚያካሄዱት ሽብርተኛነትን የማጥፋት ዘመቻ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ በተጨማሪም ለሌሎች አባላት ትምህርት ይሆናል ተብሏል፡፡
የኡጋንዳ ወታደራዊ ኃይል እንዳለው በባለፈው ወር በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት 12 ኡጋንዳውያን ወታደሮች መገደላቸውን አስታውሷል፡፡
እንዲሁም የሽብር ቡድኑ በተቀራራቢ ጊዜም በኬንያ እና ሶማሊያ ድንበር አካባቢ 9 ኬንያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ መገግደል እና ኡጋንዳ ጥቃቶችን ሲፈጽም መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡(ምንጭ: ከኒው አረብ)