በፓኪስታን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ሰዎች ሞቱ

በፓኪስታን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።

አውሮፕላኑ በመኖሪያ ሰፈር የተከሰከሰ ሲሆን፥ በውስጡ ያሉ አባላትና 12 የአካባቢው ነዋሪዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

አውሮፕላኑ በወቅቱ ለልምምድ በረራ ላይ እንደነበረና  የአደጋው መንስኤ እስካሁን አለመታወቁን ነው የሬውተርስ ዘገባ ያመለከተው።

አደጋው የደረሰበት ስፍራ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት የሚካሄድበት መሆኑ ተገልጿል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስካሁን 12 ነዋሪዎችን ከአደጋው መታደግ ችለዋል።