የሩሲያ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ መከሰቱ ተገለጸ፡፡
ፍንዳታው ሳይቤሪያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እንደተከሰተ የተገለጸ ሲሆን፣ ፍንዳታው ከተሰማ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሳይቤሪያ ከሚገኝ ወታደራዊ ጣቢያ አቅራቢያ ከሚገኙ መንደሮች ሸሽተዋል፡፡
በአቼንስክ ከተማ አቅራቢያ በተፈጠረው ፍንዳታ የአገልግሎት ሰጭ ሰራተኛን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል ዘገባው፡፡
ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሦስቱ ሆስፒታል ደርሰው ህክምና እየተደረገላቸው ነውም ተብሏል፡፡
ፍንዳታው የተከሰተበት ሥፍራ በሺዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ እንደሆነ ታውቋል። አደጋውን ተከትሎ በክራስኖያርስክ ከተማ በስተ ምዕራብ ባለው አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁም ታውቋል፡፡
(ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ሮይተርስ)