የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው አረፉ

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው አርፈዋል ።

በአውሮፓ በፖለቲካ ለረዥም ዓመታት የዘለቁት ዣክ ሺራክ ፈረንሳይን በፕሬዚዳንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋታል፡፡

ዣክ ሺራክ በሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን በፕረዚዳንትነት እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትርነት በማሸነፍ መምራት የቻሉ ሲሆን ለ18 ዓመታትም የፓሪስ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ዣክ ሺራክ የአሜሪካ መንግስት በኢራቅ የነበረው አገዛዝ ለማስወገድ ያካሄደው ጦርነት በመቃወምም ይታወቃሉ፡፡

የቀድሞዉ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጡረታ ከወጣ ከሁለት ዓመት ብሃላ ከሙስና ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው ክስ የሁለት ዓመት እስራት ተበይኖባቸው ነበር፡፡

ፓሪስ የሚገኘው የሺራክ ፋውንዴሽን የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

(ሲጂቲኤን አፍሪካ)