37 የሸኔ አባላት በምዕራብ ወለጋ ዞን እጃቸውን ሰጡ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጋንጂ ወረዳ 37 የሸኔ አባላት በሰላም ለመንግስት እጃቸውን መስጠታቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አባላቱ የክልሉ መንግስት እና አባገዳዎች ያቀረቡትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአሸባሪው የሸኔ ቡድን ለመደምሰስ አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡