381 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ተመለሱ

ሰኔ 09/2013 (ዋልታ) – 381 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረብያ ከጂዳ ከተማ  ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሽ ኢትዮጵያውያን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።