39ኛው የጃንሜዳና 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር ተካሄደ

የካቲት 6/2014 (ዋልታ) 39ኛው የጃንሜዳና 1ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር በጃንሜዳ የተካሄደ ሲሆን አሸናፊዎችም ታውቀዋል፡፡

በዚህም በወጣት ሴቶች 6 ኪሎ ሜትር ብርቱካን ወልዴ ከሲዳማ ቡና፣ መዲና ኢሳ ከአማራ ክልል እና አሳየች አይቼው አማራ ክል አሸንፈዋል፡፡

በ8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች መለሰ ብርሃኑ ከአማራ ፖሊስ፣ በረከት ነጋ ከደቡብ ፖሊስ እና ጭምዴሳ ደበሌ ከኦሮሚያ ክልል ከ1 እስከ 3ኛ ወጥተዋል፡፡

በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ጌጤ አለማዬሁ ኦሮሚያ ክልል፣ ራሄል ዳንኤል ከኤርትራ፣ እናትነሽ አላምረው ከአማራ ክልል አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ከ50 ዓመት በላይ 8 ኪሎ ሜትር አብደላ ሱሌማን፣ አያሌው እንዳለ እና ንጋቱ አጋ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ሲይዙ፤ ከ50 በታች 8 ኪሎ ሜትር ደሳለኝ ተገኝ፣ እሱባለው አስናቀ እና ተስፋዬ ያያ አሸንፈዋል፡፡

ከሩጫው መጀመር ቀደም ብሎ በባሕልና ስፓርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው የማኅበረሰብ ዐቀፍ የጤናና አካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴም ተካሂዷል፡፡