396 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ግንቦት 17/2013 (ዋልታ) – 396 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡