4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር ዘይት ዛሬ ከውጭ መግባቱ ተገለጸ

የምግብ ዘይት

መጋቢት 7/2014 (ዋልታ) 4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር የምግብ ዘይት በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ሳርቃ ለዋልታ እንደገለጹት ባቡር በመጠቀም በአንድ ቀን 4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል፡፡

ባቡሩ በአንድ ዙር 2 ሚሊዮን ሊትር እንደሚያጓጉዝ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሁንም ተጨማሪ ዘይት በባቡር በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን የምግብ ዘይት በአስቸኳይ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሆነ ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተስፋዬ አባተ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW