የዓለም ባንክ ለአፍሪካ 57 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ጠቆመ

የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ተግባር ላይ የሚውል 57 ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ  እንደሚያደርግ አስታወቀ ፡፡

ሲጂቲን ዘገበ እንደዘገበው አጠቃላይ ድጋፍ ከሚደረገው ውስጥ 45 ቢሊየን ዶላር ከአለም አቀፍ ልማት ማህበር የሚገኝ ነው ፡፡

የዓለም ባንክ የሚሰጣቸው እርዳታዎችና ብድሮች ያለወለድ  ለአለማችን ድሃ ሃገሮች የሚሰጥ መሆኑም ገልጿል፡፡   

የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም እንደገለፁት፤ የዓለም ባንክ ፋይናንስ ከሚያደርገው በጀት 8 ቢሊየን ያህሉ ለግሉ ሴክተር የሚውል ሲሆን ገንዘቡ ከአለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የተገኘ ነው፡፡

ከገንዘቡ 4 ቢሊዮን ያህሉ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት ላይ ከሚሰራውና የአለም ባንክ አካል ከሆነው  ከአለም አቀፍ የመልሶ ግንባታና ልማት ባንክ የተገኘ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ፕሬዚደንቱ እንደሚሉት አዲስ የሚቀርበው ፋይናንስ  ለትምህርት ማስፋፊያ ፕሮግራሞች፣ ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች ፣ለንፁህ ውሃና የፅዳት አገልግሎት ፣ ለግብርና፣ ለስራ ፈጠራ ፣ለመሰረተ ልማት እና ለተቋማዊ ለውጥ ስራዎች ይውላል ፡፡

ከአለም አቀፍ ልማት ማህበር የሚለቀቀው አዲሱ  ፋይናንስ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት  የተጀመሩ  448 ፕሮጀክቶችን  የሚደግፍ ይሆናል-(ኢዜአ)፡፡