በስራ ላይ ያለው የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

አሁን በስራ ላይ ያለው የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት ከመጋቢት 26/2010 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 30/2010 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ የንግድ ሚኒስቴርመግለጫ ሰጥቷል፡፡

በአለም ላይ ያለው የነዳጅ ዋጋ በሀገር ውስጥ እንዳለው ባይሆንም በሀገር ውስጥ ባለው ገበያ ላይ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር መንግስት እያከናወነ ያለውን ገበያ የማረጋጋት ስራ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ዋጋ ለቀጣይ ወር አሁን ባለው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረው 23 ብር ከ24 ሳንቲም በ85 ሳንቲም ቀንሶ 22 ብር ከ39 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ በአለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 23 ቀን 2001 ዓ.ም በተካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡

(ምንጭ: ንግድ ሚንስትር ድረ ገጽ)