ቻይና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ለማበረታታት የታሪፍ ምጣኔዋን እንደምታስተካክል አስታወቀች

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ሀገራቸው ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ለማበረታታት የታሪፍ ምጣኔዋን እንደምታስተካክል አስታውቀዋል፡፡

ቻይና በአለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ለምታስገባቸው ምርቶች የታሪፍ ማስተካከያ የምታደርግ ሲሆን፥ ሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ በእስያ ሀገራት ባአዎ የንግድ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር  ነው፡፡

በታሪፍ ማስተካከያው መሰረት በተሸከርካሪ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ቅነሳ መደረጉንም ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከውጪ ለሚገቡ ምርቶች ቻይና ያላትን ቀና እይታ ያሳየችበት ስለመሆኑና ለአለም ሀገራት ለንግድ ልውውጥም በሯን ክፍት በማድረግ ሁሉም ህዝቦች የሰፋ እድል እንዲያገኙ እንደምትሰራ በፎረሙ ላይ ገልጸዋል፡፡

መንግስታቸው የቻይና ህዝብ በስፋት የሚፈልጋቸወን ምርቶች ለማስገባትና የአለም ንግድ ድርጅት ያስቀመጠውን መስፈርት ለማሟላት ይሠራል፡፡

በዚህም የንግድ ሚዛኑን ለመጠበቅ በተመረጡ ምርቶች ላይ የታሪፍ ማንሳትና በንግድ ልውውጡ የነቃ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባቸውን ምርቶች ለማበረታታትም ቻይና አለም አቀፍ ኤክስፖ እንደምታዘጋጅ ታውቋል፡፡

ከተሸከርካሪ በተጨማሪም በፍጆታ ሸቀጦችም የታሪፍ ቅነሳ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

አጋጣሚው ቻይና የንግድ በሯን ለአለም ክፍት ለማድረግ የምታደርገውን ቁርጠኛ ጥረት የምታሳይበት ስለመሆኑም ፕሬዝዳንት ሺ አመልክተዋል፡፡ 

ያደጉት ሀገራት በንግድ ልውውጥ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ተፅዕኖ ማስቀረትና ከቻይና ጋር ያላቸውን የጠበቀ የንግድ ህግ ለቀቅ ማድረግ እንዳለባቸው ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡

ከየሀገራቱ ወደ ቻይና የሚገቡ የተመረጡ 187 ሸቀጦች ታሪፍ ከተነሳ አራት ወር ያስቆጠረ ሲሆን ፤በምግብ፤ በህክምና ቁሶች፤ በኬሚካልና አልባሳት ብሎም ሌሎች ምርቶች ላይ የነበረው ታክስ ከ17.3 ወደ 7.7 በመቶ ዝቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡

የአሁኑ የታሪፍ ቅነሳ እርምጃ ከፈረንጆቹ 2015 ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑም ታውቋል፡፤ 

በጨቅላ ህፃናት ምርቶች የነበረው የ20 በመቶ ታሪፍ ወደ ዜሮ ዝቅ የተደረገ ሲሆን የታዳጊዎች ምርትም ከ7ነጥብ5 በመቶ ታፊፍ ወደ ዜሮ ዝቅ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም የአለም ንግድ ድርጅት በ2015 ከመገናኛ ብዙሃን ምርቶች ላይ ታሪፍ ለማስቀረት የተስማማበትን ውል ተፈፃሚ ለማድረግ ቻይና ቁርጠኛ መሆኗ ተግልጿል፡፡

የታሪፍ ማስቀረት ትግበራው በቻይና ህዝቦች  ጎንግረስ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ሲፀድቅ እንደሆነ ታውቋል፡፡ (ምንጭ ፤ ሲጂቲኤን)