ህንድ ከሳኡድ አራምኮ ኩባንያ ጋር በ44 ቢሊዮን ዶላር ወጪየነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት ስምምነት አደረገች

ህንድ ከሳኡድ አራቢያው ኩባንያ ሳኡድ አራምኮ ጋር በ44 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ  የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት በጋራ ለመገንባት ስምምነት አደረገች ፡፡

ሁለቱ ሀገራት በህንድ የነዳጅ ማጣሪያን ለመገንባት የሚስችላቸውን ስምምነት አድርገዋል፡፡ ስምምነቱ በተለይም ሳዑድ አራቢያ ከኢራቅ ጋር ያላትን ፉክክር እንደሚያሳድግላት ተነግሯል፡፡

ህንድ ይፋ ባደረገችው መረጃ እኤአ በ2030 የነዳጅ አቅርቦቷን ወደ 77 በመቶ ከፍ የማድረግ እቅድ አላት፡፡ ይህም ማለት በቀን 8ነጥብ 8 ሚሊዮን በርሚል በቀን የማምረት እቅድ ይዛ ነው እየሰራች የምትገኘው፡፡

ይህንንም ፍላጎቷን ለማሳካት 44 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ፕሮጀክት ከሳውድ አራቢያው ኩባንያ ሰኡድ አራምኮ ጋር ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ እና የፔትሮሊዬም ማምረቻን ለመገንባት ስምምነት አድርጋለች፡፡

ይሀ ደግሞ ህንድን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው ለህንድ ከፍተኛ የነዳጅ ምርትን በማቅረብ የመሪነትን ስፍራ የያዘችውን ኢራቅን ለመቅደም እየጣረች የምትገኘውን ሰኡድ አራቢያን እንደሚረዳት ተነግሮላታል፡፡

 ከዚህም በተጨማሪ የሳውድ አራቢያ ኩባንያ እና የህንዱ ራትናጊሪ የነዳጅ ማጣሪያና የፔትሮኬሚካል ኮርፖሬሽን ከህንዱ ብሄራዊ የነደጅ ኮርፖሬሽን ጋር የሽርክና ስምምነት አድርገዋል፡፡

አሁን ሁለቱ ሀገራት ለመገንባት ያቀዱት ፕሮጀከት ህንድ በቀን ከ1ነጥብ2 ሚሊዮን በርሜል በላይ በቀን የማጣራት አቅም እንዲኖራት የሚያደርጋት ሲሆን በዓመት ደግሞ ከ18 ሚሊዮን ቶን በላይ የተጣራ ነዳጅ እና ፔትሮሊየም እንድታመርት ይረዳታል፡፡

ፕሮጀክቱ አሁን በዓለም ላይ በነዳጅ ፍላጎታቸው ከፍተኛ እድገትን እያስመዘገቡ ካሉት ሀገራት ከሚያስገነቡት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከልም አንዱ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡

የሳዑድ አራቢያው ኩባንያ ሰኣዱ አራምኮ ፕሮጀክቱ ስራ ሲጀምር በፕሮጀክቱ የሚመረተውን ነዳጅ 50 በመቶውን ድፍድፍ ነዳጅ እንደሚያቀርብ ተገለፀ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ኩባንያው በአዲስ ስትራቴጂ የፕሮጀክቱን 50 በመቶ ትርፍ ተቋዳሽ ሊሆን የምችልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራም እንደሚሰራ ተገልፆኣል፡፡

በዓለም ሶስተኛ የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያ እንደሆነ የሚነገርለት የሳኡድ አራቢያው ኩባንያ እያደገ የሚገኘውን የነዳጅ ፍላጎት የማዳረስ እቅድም ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህም የህንዱ አዲሱ ፕሮጀከት የዚህ ማሳያ የሚሆን ነው የተባለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሳኡድ አራቢያ ከፍተኛ የድፍድፍ ነዳጅ አቅራቢ ሊያደርጋት የሚስችላትን ከባለፈው ዓመት ቢሊዮን ገንዘብ በማሌዢያ እና በህንድ ብቻ ኢንቨሰት እያደረገች ትገኛለች፡፡

ሳኡድ አራቢያ ለህንድ ተቀናቃኝ የሌለው የነዳጅ አቅራቢ የመሆን ፍላጎት ያላት ሲሆን በዚህም በኢራቅ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ገብታ እንደምተገኛ ነው የተነገረው፡፡

ሰዑድ አራቢያ ይህነ አንግባ መጓዝ ከጀመረች በኋላ ኢራቅ በህንድ ውስጥ ያላትን የበላይነት በመጠኑም ቢሆን እያጣች መምጣቷን ያስነበበው ሮይተርስ ነው፡፡