ሚኒስቴሩ በሩብ ዓመት መሰብሰብ ከነበረበት ገቢ 10 ቢሊዮን ብር ያህል መሰብሰብ አለመቻሉን አስታወቀ

የገቢዎች ሚኒስቴር በመጀመሪያው ሩብ ዓመት መሰብሰብ ከነበረበት ገቢ 10 ቢሊየን ብር ያህሉን መሰብሰብ አለመቻሉን አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከሀገር ውስጥ ገቢና ከጉምሩክ ቀረጥ ለመንግስት ማስገባት የነበረበትን 10 ቢሊዮን ብር አለመሰብሰቡን ነው ይፋ ያደረገው።

ሚኒስቴሩ ባለፉት ሶስት ወራት 54 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ቢያቅድም ያሳካው 44 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው።

የሩብ ዓመት እቅዱ ያልታሳካው በግብር ከፋዩ ዘንድ በሚታዩ ክፍተቶችና በዋነኛነት በተቋሙ የአሠራር ሥርዓት ጉድለት ነው ተብሏል ።

የገቢዎች ሚኒስቴር በያዝነው 2011 ዓ.ም 213 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ ገቢና ከጉምሩክ ቀረጥ ለመሰብሰብ አቅዷል።(ኢዜአ)