አዲስ አበባ በመግባት ላይ የነበረ 919 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

በህገወጥ መንገድ በተሸከርካሪ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ የነበረ 919 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በተሸከርካሪ ሊገባ የነበረው ህገወጥ የጦር መሳሪያው ቱርክ ሰራሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምርመራ እያደረገበት ይገኛል ተብሏል፡፡

ህገወጥ የጦር መሳሪያው በዛሬው ዕለት መያዙን የየካ ወረዳ ሰባት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ገልጿል፡፡