ከ200 በላይ አምራቾችና ሻጮች በኢድ ኤክስፖ ላይ ተገኝተዋል

በዘንድሮዉና 8ተኛዉ የኢድ ኤክስፖ ከ200 በላይ የሀገር ዉስጥና የዉጭ አምራቾችና ሻጮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኤክስፖዉ እስከ ግንቦት 27 የሚቆይ ሲሆን ከ 60ሺ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የተለያዩ የጎንዮሽ ዝግጅቶችም እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የዘንድሮዉ ኢድ በዓል በሙጅሊሱ ዘንድ የነበረዉ ክፍፍል ህዝበ ሙስሊሙን ሊያስማማ በሚችል መልኩ  በእርቅና ይቅርታ መፈታቱ ትልቅ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡