ብራዚል ማረሚያ ቤቶቿን በፋሽን ዲዛይን እያደመቀች ነው

አብዛኛውን ጊዜ የፋሽን ትዕይንቶች ለዕይታ የሚበቁት በተመረጡ ዲዛይነሮችና ቅንጡ ቦታዎች ቢሆንም ከሰሞኑ በብራዚሏ ከተማ ሳኦ ፖሎ በማያፈናፍነው አድሪያ ማሬይ ማረሚያ ቤት ትዕይንቱ ቀርቧል።

ሌላ ግዜ ታራሚዎቹ የሚያስተናግደው ማረሚያ ቤት ከሹራብ በተሰሩ ደማቅ ቀለም የለበሱ ሞዴሎች አድምቀውታል። 
ልብሶቹን ዲዛይን ያደረጉት ታራሚዎቹ ሲሆኑ፣ ይህ ያልተለመደው ትዕይንትም የተሃድሶው ፕሮግራም አካል እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ታራሚዎቹ የሹራብ አሰራር ጥበብን ለመማር የዚህ ፕሮግራም አካል ከሆኑ የአስራ ሁለት ሰአት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ አንድ የእስር ቀን ይቀነስላቸዋል።