በበጀት ዓመቱ በጉምሩክ ኮሚሽን ግምታቸው ከ1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል

የገቢዎች ሚኒስትር በበጀት ዓመቱ በጉምሩክ ኮሚሽን ግምታቸው ከ1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ

በዘንድሮ ዓመት በጉምሩክ ኮሚሽን በገቢ ኮንትሮባንድ በበጀት ዓመቱ በተቋሙ ስር ባሉ 14 ቅ/ጽ/ቤቶች በተከናወነ የኮንትሮባንድ መከላከል ስራ ግምታዊ ዋጋቸው 1ቢሊዮን 298ሚሊዮን 765ሺ 042 ብር የሆነ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

በዚህ መሰረት አዲስ አበባ ኤርፖርት 334 ሚሊዮን 488ሺ 287 በመያዝ የመጀመሪያዉን ድርሻ ይዘዋል ተብሏል፡፡

በተከናወነው ኮንትሮባንድን የመከላከል ስራ አዳዲስ አልባሳት፣ የኤሎክትሮኒክስ እቃዎች፣ አደንዛዥ ዕጽ፣ ምግብና መጠጦች፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም እንደሚገኙበት የገቢዎች ሚኒስቴር  ለጣቢያችን በላከው መረጃ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ኤርፖርት 334ሚሊዮን 488ሺ 287፣ ሀዋሳ 165ሚ 558ሺ 711 ጅግጅጋ 165ሚሊዮን 406ሺ 469፣ ሚሌ 160ሚሊዮን 127ሺ162፣ ሞያሌ 126ሚሊዮን 139ሺ168፤ አ.አቃሊቲ 114ሚሊዮን 263ሺ ኮምቦልቻ 62ሚሊዮን 413ሺ 490፣ ድሬደዋ 60ሚሊዮን 953ሺ 637፣ ባህርዳር 34ሚሊዮን 852ሺ 800፣ አዳማ 25ሚሊዮን 814ሺ 244፣ መቀሌ 17ሚሊዮን 775ሺ 055፣ ጋላፊ 14ሚሊዮን 563ሺ 114፣ ጅማ 14ሚሊዮን 195ሺ 754 ነዋናመ/ቤት 2ሚሊዮን 214ሺ ብር የሚገመቱ የተለያዩ እቃዎች በበጀት ዓመቱ መያዛቸውንየገቢዎች ሚኒስቴር  ለጣቢያችን በላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።