44ኛው የካራማራ የድል በዓል እየተከበረ ነው

የካቲት 26/2014 (ዋልታ) 44ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የካራማራ የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡

የካራማራ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በመታሰቢያ በዓሉ የኩባ አንባሳደር የአዲስ አበባና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባለት እንዲሁም የካራማራ ጀግኖች ሰማዕታት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ድሉ የዚያድባሬ ጦር ኢትዮጵያን ለመውረር ሲሞክር የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኩባ ወታደሮችም የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር ካራ ማራ ላይ ድል በማድረጉ የተገኘ ነው፡፡