44 ኢትዮጵያውያን ከቤይሩት ተመለሱ

ግንቦት 21/2013 (ዋልታ) – ከሊባኖስ ቤይሩት 44 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቀ።

ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንዳመላከተው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተወካዮች በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።