440 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ተመለሱ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – 440 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን እንዲመለሱ እየተደረገ ባለው ጥረት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 207 ህጻናትና 233 ሴቶች በአጠቃላይ 440 ኢትዮጵያዊያን መመለሳቸውን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።