ባንኩ ከ2ሺህ 800 ለሚሆኑ ዜጎች የዓይን ንቅላ ተከላ ማድረጉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ይህንን ያከናወነው ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ውስጥ ሲሆን በጥቅሉ 2 ሺህ 800 የአይን ንቅለ ተከላ አከናውኗል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የባላደራ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ዳንኤል ገብረ ሚካኤል  በንቅለ ተከላው ዜጎች ብረሀናቸውን ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የአስራ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል በዛሬው እለት ተከብሮ ውሏል፡፡

የዓይን ባንኩ አሰባስቦና አዘጋጅቶ የሚያሰራጫቸው ብሌኖች ጥራታቸውን የጠበቁ ለማድረግ ባደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ ስራዎችን እየራ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በዚህም አለም አቀፍ እውቅና አግኝቶ የምስክር ወረቀት እንደተሰጠው ማወቅ ተችሏል ።

በብሌን ጠባሳነት ምክኒያት ማየት ለተሳናቸው ዜጎች ብረሀን ለመሆን በሂወት ዘመናቸው ቃል የገቡና ሂወታቸው ሲያልፍም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በማሳወቅ የዓይን ብሌን ለመሰብሰብ የሚደረገውን ጥረት አንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል ።

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የባላደራ ቦርድ ጸሀፊ ዶክተር መነን አያሌው ናቸው፡፡ ብሌናቸውን በመለገስ ትብብር ላደረጉት ምስጋና አቅርበዋል፡፡(ምንጭ: የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር )