ከልክ በላይ መተኛት ለበሽታዎችና ለሞት እንደሚዳርግ ጥናት አመላከተ

ከልክ በላይ መተኛት የለሽታዎች ተጋላጭነትን እንደሚጭምርና ለሞት እንደሚዳርግ አንድ ጥናት አመላክቷል፡፡

ጎልማሳ የተባለ ሰው በአንድ ለሊት ከ6 እስከ 8 ሰዓታት መተኛት እንዳለበት የህክምና ባለሞያዎች የሚመክሩ ሲሆን ከዚህ በላይ ጊዜያቸውን በእንቅልፍ የሚያሳልፉ ሰዎች ግን ለልብ በሽታ ተጋላጭነትና ለሞት አደጋ የመዳረግ ዕድልን እንደሚጨምር ነው የተመለከተው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥናቱ በ21 ሀገራት ባካሄደው ምርምር ከ8 ሰዓታት በላይ መተኛት ለልብ በሽታ፣ ለድንገተኛ የአንጎል ደም መፍስስ/ስትሮክ/ እና የሞት አደጋ ተጋላጭነትን በ41 በመቶ እንደሚጨምር ዩሮፕያን ሄርት ጆርናል የተሰኘው በአውሮፓ የልብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መጽሄት የዘርፉን ተመራማሪዎች ዋቢ በማድረግ ዘግቧል፡፡

ምሽት ከስድስት ሰዓታት በላይ ተኝተው በቀን ውስጥ ድጋሚ ለተወሰነ ጊዜ የሚያሸልቡ ሰዎች እንደዚሁ ከላይ ለተጠቀሱት የጤና እክሎች ተጋላጭ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

በመተኛ ሰዓታት ውስጥ ከ6 ሰዓታት በታች መተኛት ለተለያዮ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን በ9 በመቶ እንደሚያሰፋም ጥናቱ አመላክቷል፡፡ (ምንጭ፦ሲ.ኤን.ኤን)