ዓለም አቀፉ የጥናትና ምርምር ተቋም በሽታዎች ያሉበትን ደረጃ የሚያሳውቅ መሣሪያ ይፋ አደረገ

አለም አቀፉ የጥናትና ምርምር ተቋም አይቢኤም በሽታዎች ያሉበትን ደረጃ ማወቅ የሚያስችል በእጅ ጣት ላይ የሚገጠም መሳሪያ ይፋ አድርጓል፡፡

መሳሪያው በተለይም ሰውነትን ለማንቀሳቀስ የሚረዳውን የአዕምሮ ክፍል ላይ የሚደርስ እክልን ወይም ፓርኪንሰን የተሰኘውን በሽታ ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ የዋሉ መድሓኒቶች ውጤታማነት ለማወቅ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

በአለም ላይ በሚገኙ 6 አህጉሮች ከ3ሺ በሚልቁ ተመራማሪዎቹ ግዙፍና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን የሚከውነው አይቢኤም በሰዎች የእጅ ጣት ጥፍር ላይ የሚገጠም መሣሪያ ይፋ አድርጓል፡፡

ይህ መሣሪያ ፓርኪንሰን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችም የሚያመጡአቸውን የህመም ምልክቶችን ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ ጥቅም ላይ የዋሉ መድሃኒቶችን ውጤታማነት ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡

መሳሪያው በእጅ ጣቱ ጥፍር ላይ የተገጠመለት ሰው ስራዎችን በሚከውንበት ሰአት  የጥፍሩን እንቅስቃሴ በመከታተል ውጤቱን መተንተን የሚያስችል መተግበሪያም ተገጥሞለታልም ነው የተባለው፡፡

ከዚህም ባሻገር  ሴንሰሩን  ከሰውነት ቆዳ ጋር በማያያዝ በመተግበሪያው አማካኝነት  የጡንቻዎችንና ነርቮችን ጤንነት ለማወቅ እንደሚረዳ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

ይሁንና ተመራማሪዎቹ በቆዳ ላይ የሚገጠሙ መሳሪያዎች ኢንፌክሽኖችንወይም ቁስለትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ችግሮችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በመጠቆም የእጅ ጥፍር እንቅስቃሴን ብቻ በመመልከት መረጃን ለማወቅ መቻል የተሻለው አማራጭ እንደሆነና እነሱም በጥፍር ላይ የሚገጠመውን መሳሪያ የሰሩት ይህንን ጉዳት ለመቀነስ አስበው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡

የምርምር ቡድኑ መሳሪያው የፓርኪንሰን በሽታን በስኬታማ ደረጃ ለማወቅ እንዳስቻለው ሁሉ  ሌሎችንም የበሽታ አይነቶች በተሳካ ሁኔታ ለመለየት እንደሚያስችል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡

ይሁንና መሳሪያው መቼ ለገበያ እንደሚቀርብ ግን ለመናገር ተቆጥበዋል ይለናል ቴክ ክረንች ያስነበበው መረጃ ነው፡፡