በኩፍኝ ህመም ተጠቂ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

በኩፍኝ ህመም ተጠቂ የሚሆኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የክትባት ጉዳዮች ደይሬክተር ካትሪን ኦብራይን በፈረንጆቹ 2ዐ17 የነበረውና ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑት ሰዎች ቁጥር 173 ሺህ ሲሆን በ2ዐ18 ወደ 23ዐ ሺህ ማደጉን ገልፀዋል፡፡

እየተስፋፋ ያለውን ችግር የዓለም አገራት በክትባት እንዲከላከሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የበሽታው ክትባት መስጠት የተጀመረው ከፈረንጆቹ 196ዐዎቹ ጀምሮ ቢሆንም በህክምና ዕጦት በርካቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-ዩኤን ኒውስ)