የካንሰር ህክምና መመሪያ ተዘጋጀ

የካንሰር ህክምና የአገልግሎት ጥራት ደረጃውን ጠብቆና ወጥነቱን አረጋግጦ እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጀ፡፡

መመሪያውን የሚያስተዋውቅ አውደ ጥናት በተካሄደበት ወቅት ውይይቱን የመሩት የክቡር ሚኒስትር ዴኤታዋ አማካሪ አቶ ግርማ አሸናፊ መመሪያው የተዘጋጀው ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጀምሮ እስከ ክልል ጤና ቢሮና ሌሎች የጤና ተቋማት የሚዘልቅ የውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል ፡፡
በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አስተባባሪ ዶ/ር ሶስና ሀይለማርያም በበኩላቸው የተዘጋጀው መመሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰራበትና በተግባር መመሪያ ያላቸውን ሀገሮች በሞዴልነት በመውሰድ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀው ለተግባራዊነቱ የሚመለከታቸው ሁሉ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በዕለቱ ከኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር፣ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ሆስፒታሎች እንዲሁም ከአጋር አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች በመመሪያው ዙሪያ ተወያይተው አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡