የጤና ዘርፍ ተመራማሪዎች የልምድ ልውውጥ አካሄዱ

አርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም በጤናው ዘርፍ የምርምርና የፈጠራ ግኝቶችን ለሚሰሩ ተመራማሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ ።

በጤና ሚኒስቴር የሚደገፍ ግራንድ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የምርምርና የፈጠራ ግኝቶችን ለሚሰሩ ተመራማሪዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂዷል፡፡/የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር/

የአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ገነቱ የምክክር መድረኩን በከፈቱበት ወቅት ለሀገራችን የጤና ችግር በሀገር ልጅ ሀገር በቀል ፈጠራና መፍትሄ ማበጀት የሚያስችለውን የምርምርና የፈጠራ ሰራዎችን ለመደገፍ አንድ መቶ ወጣት ተመራማሪዎች የፈጠራና የምርምር ስራዎቻቸውን ለውድድር አቅርበው አስሩ መመረጣቸውን ገልጸዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ የተመረጡት ተመራማሪዎች በሀገራችን ከሚገኙ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ተቋማት የተውጣጡ ሲሆን ተስፋ ሰጪ የምርምር ስራዎቻቸውን ማቅረባቸው ተናግረዋል፡፡

በምክክር መድረኩም የመጀመሪያው ዙር ተመራማሪዎች በምርምር ስራዎቻቸው ያጋጠማቸውን መልካም ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶችን ለሁለተኛው ዙር ተመራማሪዎች አካፍለዋል፡፡

የአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም ለወጣት ፈጣሪዎችና ተመራማሪዎች የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡