የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲን ለማሻሻል ውይይት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲን ለማሻሻል የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲን ለማሻሻል በቀረበው አዲስ የጤና ፖሊሲ ረቂቅ ላይ የጤና ሚኒስቴር ከክልል የጤና ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ25 አመታት በላይ የቆዬውን የጤና ፖሊሲ ማሻሻል የሀገርን አቅምና ዕድገት ምጣኔን ታሳቢ በማድረግ የህዝብን ፍላጎት የሚያሟላ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላልም ነው የተባለው፡፡