በኢትዮጵያ ለ5 ዓመታት የሚያገለግል አገራዊ የጤና ደህንንት ትግበራ እቅድ ይፋ ሆነ

ከ2009 ዓ.ም ህዳር ወር ጀምሮ ሲዘጋጅ የነበረው አገራዊ የጤና ደህንነት ትግበራ ዕቅድ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡

ዝርዝር እቅዱን ለመተግበር ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ገንዘቡ በኢትዮጵያ መንግስትና በአጋር ድርጅቶች እንደሚሸፈንም ተነግሯል፡፡

አገራዊ የጤና ደህንነት ትግበራ ዕቅድ እ.ኤ.አ እስከ 2023 ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል፡፡