የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈረመ።

ስምምነቱ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መካከል ነው የተፈረመው።

ስምምነቱንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን እና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ አበባየሁ ናቸው የፈረሙት።

ስምምነቱ በሀገገሪቱ ያለውን የህክምና መሳሪዎችን ፍላጎት ለማሟላትና ለግዢ የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል።

ኢትዮጲያ ለህክምና መሳርያዎች ብቻ በዓመት እስከ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደምታደርግ መኘረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዛሬው እለት የተፈረመው የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ወደ ስራ ሲገባ ሀገሪቱ በዓመቱ ለህክምና መሳሪያ ግዢ የምታወጣውን ወጪ ይቀንሳል ተብሎ ታምኖበታል።

ምንጭ፡- ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር