ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ የጊኒወርም ባለመታየቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ላለፉት አንድ አመት ተኩል ጊኒወርም በሰው ላይ ባለመታየቱ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ የኢትዮጵያ መንግስት ጊኒ-ወርምን ጨርሶ ከኢትዮጵያ ለማስወገድ እየሰራ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በበኩላቸው ጊኒ ወርምን ከኢትዮጵያ ጨርሶ ለማስወገድ መንግስት ተግቶ እየስራ መሆኑን ጠቀሶ የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል፡፡