የደም ግፊትን መቆጣጠር የስትሮክ ተጋላጭነትን 20% ይቀንሳል

የደም ግፊትን በመቆጣጠር ብቻ የደም ግፊት ተጋላጭነተን በ20 በመቶ እንደሚቀንስ አዲስ የወጣ ጥናት አመልክቷል።

በበጃፓን ቶክዩ ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ የደም ግፊት መጠንን በመቆጣጠር ብቻ ለሁለተኛው አይነት የስትሮክ አይነት ተጋላጭነትን የሚቀንሰው።

የጥናት ቡድኑ መሪ የሆኑት ዶክተር ካዞው ኪጋታዋ፥ ለሁለተኛው አይነት ስትሮክ የመጋለጥ እድልን ለመቀነስ ቢያንስ ቢያንስ የደም ግፊታችንን 130 በ80 ላይ ማቆየት መልካም ነው ብለዋል።

ከተቻለ ደግሞ የደም ግፊታችንን ጤናማ ተብሎ በተቀመጠው 120 በ80 ላይ ማቆየት መቻል ደግሞ የበለጠ ተመራጭ መሆኑንም ነው ዶክተር ካዞው ኪጋታዋ ያስታወቁት።

የደም ግፊታችንን ለመቆጣጠር ደግሞ የህክምና ባለሙያዎችን በማማከር የሚታዘዝልንን መድሃኒት እና ሌሎች አማራጮች መከተል መልካም እንደሆነም ነው ጥናቱ ያመላከተው።

የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚታዘዙ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሁም ጥንቃቄ የተሞላበት የህክምና ክትትል ማድረግ መልካም እንደሆነም ነው ያስታወቁት።