በቱርክ በእግርና በእጃቸዉ የሚሄዱ ሰዎች ጉዳይ ለሳይንሱ እንቆቅልሽ ሆኗል

በቱርክ አንድ ራቅ ያለ ገጠራማ አካባቢ እዉነትም በሁለት እጅና እግራቸዉ  የሚሄዱ አንድ ቤተሰብ እዉነታ ከአለም በስተጀርባ ተደብቋል፡፡

ክስተቱን በእ.አ.አ 2018 60 ደቂቃ በተሰኘ የአዉስትራሊያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለአለም እስኪያሰራጨዉ ድረስ እንዲህ አይነት ታሪክ ይኖራል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡

ርጂት ኡላ ይሰኛሉ፡፡ከባለቤታቸዉ 18 ልጆችን ወልደዋል፡፡ታዲያ ከእነዚህ ልጆቻቸዉ ዉስጥ 12ቱ ጤነኞች ሆነዉ ነዉ የተወለዱት፡፡ስድስቱ ግን ለየት ካለ የአካል ጉዳት ጋር ተወለዱ፡፡በመጀመሪያ ጉለን የተሰኘዉ ልጃቸዉ ላይ ነበር ይህ የአካል ጉዳት የታየዉ፡፡ይህም ሲራመድ ልክ እንደሰከረ ሰዉ ይንገዳገዳል፡፡እንደዛም ሆኖ ግን ቆሞ ነዉ የሚራመደዉ፡፡ቀሪዎቹ እህት ወንድሞቹ ግን ልክ እንደ ሌሎች እንስሳ አጎንብሰዉ በእጅና እግራቸዉ መራመድ ጀመሩ፡፡

ይህ ለየት ያለና በዚህ ቤተሰብ ላይ የታየ ክስተት ለቤተሰቡ የፈጣሪ እርግማን ነዉ ብለዉ ደምድመዋል፡፡ለተመራማሪዎች ግን ሳይንሱ ያልመለሰዉ ሚስጥር ሆኗል፡፡

የአጅት ልጆች በህፃንነታቸዉ ልክ እንደ ማንኛዉም ህፃን ዳዴ ብለዋል፡፡ከ9 ወራት በኋላ ግን መቆም ሲያቅታቸዉና ልክ ዳዴ ሲሉ እንደነበረዉ በዛዉ መራመድ እንደቀጠሉ ይናገራሉ፡፡

በቱሪክ ሜዲካል መፅሄት ጉዳዩን ያነበቡትና የዝግመት ለዉጥ ስነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት  ፕሮፌሰር ኒክ ሃፍሪ  በበኩላቸዉ፤ መጀመሪያ ጉዳዩን ሲሰሙ በጣም ማመን እንደተቸገሩና እንዲህ አይነት ክስተቶች ሳይንቲስቶች በህይወት ዘመናቸዉ ከሚያጋጥማቸዉ ሚስጢራዊ ክስተት አንዱ ነዉ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

በዚህ የአካል ጉዳት የተጠቁት የአቶ አጅት ልጆች ከ18 አስከ 34 አመት ባለዉ የእድሜ ክልል ዉስጥ ይገኛሉ፡፡

ከህፃንነት የእድሜ ዘመን ዉጪ ነብስ ባወቁ ሰዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ክስተት በተለይ በሳይንሱ ታሪክ ተሰምቶ እንደማይታወቅና ክስተቱ የመጣዉ ምናባትም ሚዛን ለመጠበቅ ትእዛዝ የሚሰጠዉ የአእምሮ ክፍላቸዉ ላይ ችግሩ ተከስቶ ሊሆን እንደሚችል ግን ተመራማሪዎቹ መላምታቸዉን ያስቀምጣሉ፡፡

ነገር ግን ይህንን ሃሳብ የሚጻረር ደግሞ አንዳንዴ ይህ የአእምሮ ክፍል ሳይኖራቸዉ የተወለዱ ሰዎች እንኳን ቆመዉ መሄድ መቻላቸዉ ደግሞ የክስተቱን መንስኤ ሚስጥራዊ ያደርገዋል፡፡

የሚገርመዉ ነገር ይህ መንስኤዉ ያልታወቀ የአካል ጉዳት በእነኚህ ሰዎች ህይወት ተፅእኖዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ከማንኛዉም ማህበራዊ ኑሮ ተገልለዉና ህፃን አዋቂ እየሰደባቸዉ እንዲኖሩ አድርጓቸዋልና፡፡

ፕሮፌሰር ኒክ ሃፍሪ ግን ይህንን ሁኔታ መቀየር የሚያስችል ሙከራ ለመጀመሪያ ጊዜ በማድረግ አስገራሚ ዉጤት ችለዋል፡፡

የአቶ አጅት ልጆችም ይህንን መደገፊያ ምርኩዝ በመጠቀም ቆሞ ለመሄድ ሙከራ አደረጉና አበረታች ለዉጥ ማሳየት ቻሉ፡፡

ቆሞ መራመድ የማታሰብ የማይመስላት የአቶ አጅት ልጅ ከዚህ በኋላ በደንብ ቆሜ መሄድ ከቻልኩኝ ዳንሰኛ መሆንና ማግባት እንደምትፈልግ ተናግራለች፡፡ 60 ሚኒትስ አውስትራሊያ ነው የዘገባው ምንጭ፡፡