ባለ አንድ ቴራ ባይት ሚሞሪ ካርድ

መረጃዎችን በመጫን አቅሙ ከፍተኛ የተባለው ባለ አንድ ቴራ ባይት ሜሞሪ ካርድ ተመረተ፡፡

ሜሞሪ ካርዱን ያመረተው ሳንዲስክ የተሰኘው ኩባያ ሲሆን የካርዱ የመጫን አቅም አንድ ቴራ ባይት(አንድ ሺ ጊጋ ባይት) ነው፡፡

ይህም ከአሁን ቀደም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ሲሆን በሜሞሪ ካርድ ታሪክ በቀዳሚነት ለመሰለፍ በቅቷል፡፡

ብዙዎችን አጃኢብ ያሰኘው ሚሞሪ ካርድ 16 ጊጋ ባይት የመያዝ አቅም ካላቸው 50 የአይ ፎን ሞባይሎች የመጫን አቅም ጋር ይስተካከላል፡፡

ሳንዲክ ከዚህ ቀደም 512 ጊጋ ባይት የመጫን አቅም ያለው ሚሞሪ ካርድ አምርቶ ለገበያ አቅርቦ ነበር፡፡

በወቅቱም 800 ዶላር ዋጋ ተቆርጦለት ለገበያ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

አዲሱ ሚሞሪ ካርድ በስንት ዶላር ለገበያ እንደሚቀርብ የተቆረጠለት ዋጋ ባይኖርም ቀድሞ ለገበያ ከቀረበው በተሻለ ዋጋ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ- ፖፑላር ሳይንስ