ከመርከቦች የሚጣሉ ፕላስቲኮች በውሃ ብዝሃ ህይወት ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው

ከመርከቦች የሚጣሉ ፕላስቲኮች በውሀ ብዝሀ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው ተገለጸ ፡፡

ጉዳቱ በተለይ የባህር አእዋፋት ላይ የባሰ እየሆነ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የአካባቢ ብክለት ለመታዘብ ቢ ቢ ሲ በአውስትራልያ አንድ ደሴት ላይ ቅኝት አድርጓል፡፡

በቅኝቱም በአውስትራሊያ ሎርድ ሆዊ ተብላ በምትጠራው ደሴት ላይ የሰው ልጅ በማወቅም ባለማወቅም በባህር ላይ የሚጥላቸው የፕላስቲክ እቃዎች በባህሩ መኖሪያው ያረጉት ብዝሀ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው ይዞት በወጣው መረጃው አመላክቷል፡፡

ጉዳቱ በደሴቲቱ ባህር ላይ ሌሎች የባህር አካላት ለማደን አሰሳ የሚያደርጉት አእዋፋት እጅግ የከፋ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ከምስራቃዊ አውስትራሊያ 600 ኪሎሜትር ርቀት ባለው ደሴት የሚኖሩት አዕዋፋቱ በባህሩ ውስጥ የሚገኙት አካላት እና የፕላስቲክ ቁርጥራጮች መለየት ባለመቻላቸው ችግሩን አሳሳቢ እንዳደረገው መረጃው ያትታል፡፡

አእዋፋቱ በብዛት የሚያገኙት የፕላስቲክ እቃ ሲለሚመገቡ ለሞት መዳረጋቸው እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ነው የተጠቆመው፡፡

በዘርፉ ጥናት እያካሄዱ የሚገኙት የስነ ህይወት ተማራማሪ ዶክተር ጄኒፈር ላቨርስ ‹‹በጣም አሳዛኝ ሀቅ ነው፤ከአንድ ወፍ የሚወጣው የፕላስቲክ ቁርጥራጭ ብትመለከቱ የማይታመን ነው፤እስካሁን ከአንድ በህይወት ከሌሉ ወፎች በአማካይ ከ90 እስከ መቶ የፕላስቲክ ቁርጥራጮች ነው ከሆዳቸው እየወጣ የሚገኘው፡፡›› በማለት ገልጸውታል፡፡

የአውስትራልያ ተማራማሪዎች በዘርፉ የተለያዩ ሥራዎች እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን ነፍስ ውጪ ግቢ እያሉ የሚገኙት ወፎችም በህይወት የማትረፍ ሥራዎች እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ሌቨጅ የሚል ስያሜ ያለው ዘዴ እየተጠቀሙ እንደሚገኙም መረጃው አመላክቷል፡፡ዘዴው በወፎች ሆድ እቃ የሚገኘው የፕላስቲክ ንጥረ ነገር በማጠብ የሚያስወግድ ነው ተብሏል፡፡

በሎርድ ሀዊ ያጋጠመው ከፍተኛ የባህል ብክለት በብዙ የውሃ አካላት እያጋጠመ እንዳለ ያመላከተው ዘገባው በተለይ በባህር ትራንስፖርት የተሰማሩ አካላት ሊያስቡበት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡