በዓለማችን የመጀመሪያው ተጣጣፊና ተሸከርካሪ ኮምፒዩተር ተሰራ

በዓለማችን የመጀመሪያው ተጣጣፊና ተሸከርካሪ ኮምፒዩተር መሰራቱ ተገለጸ፡፡

በተለያየ ጊዜ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እየታከለባቸዉና ተሻሽለዉ እየተሰሩ የሚመጡ የኢሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ነዉ፡፡

አሁን የተሰራዉ የኮምፒውተር ደግሞ እስከዛሬ ከተሰሩት የኮምፒተር አይነቶች የተለየና ልክ እንደ ሶፍት የሚጠቀለል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ሂዩማን ሚዲያ ላብ በተሰኘዉና በካናዳ ኪዩንስ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ የተሰራዉ ይህ ተሸከርካሪና ተጣጣፊ ኮምፒውተር 7 ነጥብ 5 ኢንች ስክሪን ያለዉ ሲሆን በኮምፒውተሩ ሁለት ጫፎች ላይ ባሉት ማሽከርከሪያ መዘዉሮች  በመጠቀም ተጠቃሚዉ የኮምፒውተሩን ስክሪን በፈለገዉ ልክ በማሳደግ እና በማሳነስ መጠቀም ይችላል፡፡ 

በዚህ ተጣጣፊና ተሽከርካሪ ኮምፒውተር ጫፉ ላይ ባለዉ መዘዉር በአንድ እጅዎ ብቻ በመጠቀም ጥሪ ማስተላፍ ያስችላል፡፡

ይህ ኮምፒውተር እስከመጨረሻ በማሽከርከር አነስተኛ መጠን እንዲኖረዉ በማድረግ በቀላሉ በኪስዎ ይዘዉ መንቀሳቀስም ይችላሉ ነዉ የተባለዉ፡፡

ይህ ልክ እንደ ሶፍት የሚጠቀለል ኮምፒውተር ጥሪ ማስተላለፍም ሆነ ጥሪ መቀበል በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲዎችንም መጠቀም ያስችላል ነው የተባለው፡፡

የዚህ ኮምፒውተር ፈጠራ ኩባንያ ዳይሬክተር ሮኤል ቨርቴጋል በበኩላቸዉ ይህ ተሸከርካሪ ኮምፒውተር ረዘም ያለ ሰዓት ስክሪኑን እየተጠቀሙ መቆየት የሚያስችል በመሆኑና በጣም ፈጣን በሚባል ደቂቃዎች የፈለጉትን ያህል መጠቀም የሚያስችል በመሆኑ እንዲሰሩት አነሳስቶናል ብለዋል፡፡

ኮምፒተሩን ሳያሽከረክሩ ስክሪኑን ዘርግቶ በሙሉ ስክሪን መጠቀም ያስችላል ነዉ የተባለዉ፡፡

እንደ ሳምሰንግና ሞርቶዴላ ያሉ የስልክ አምራች ኩባያዎች ተጣጣፊ የእጅ ስማርት ስልኮችንና ኮምፒውተሮችን አምርተዉ ለገበያ አስተዋዉቀዋል፡፡

አሁን የተሰራዉ ተጣጣፊ ኮምፒውተር ግን ቀደም ሲል ከተፈበረኩት የተለየና ሙሉ በሙሉ በመጠቅለል የተለያዩ አገልግሎቶችን ማስጠቀም የሚያስችል ነዉ፡፡

በኮምፒውተሩ ጫፍ ላይ ያለዉን መዘወሪያ በመጠቀም ወደ ፈለጉት አቅጣጫ እያሽከረከሩ መጠቀም የሚያስችል ምርጥ የቴክኖሎጂ ዉጤት ተብሏል፡፡ (ምንጭ፤ሚረር ኦንላይን)