ናሳ የዓለም በረዶን መቅለጥ መጠን የሚለካ የሌዘር ሳተላይት አስወነጨፈ

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም/ናሳ/ የአለምን የበረዶ መቅለጥ መጠን ለመለካት የሚያስችል የሌዘር ሳተላይት አስወነጨፈ፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ  በምድራችን ላይ እያስከተለው  ያለውን ተፅዕኖ ተከልትሎ የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም/ናሳ/ በፕላኔታችን ላይ የሚገኙ  የበረዶ ሽፋኖችንና የበረዶ ግግሮች ያሉበትን ሁኔታ ለማጥናት የሚያስችለውን  የሌዘር ሳተላይት ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማስወንጭፍ ችሏል ፡፡    

የናሳ የጠፈር ምርም ቡድን ከካሊፎርኒያ ዴልታ 2 የተባለች ጭረር ለቃቂ ሳተላይት ወደ ጠፈር በመላክ በመሬት ዙሪያ እየጨመረ ያለውን የባህር ከፍታ ለመከታተል የሚያስችላቸውን ስራም ጀምሯል፡፡
 

በመላው ዓለም እየጨመረ ያለውን የባህር ከፍታ ለመከታተል እንዲሁም የበረዶ ግግርና የበረዶ ሽፋኖች እንዴት በፍጥነት እንደሚቀንሱ ለመለካት የጨረር ለቃቂ ሳተላይት መሳሪያዎችን መጠቀም ግድ ይላል ፡፡

መሳሪያው በመሬት ዋልታዎች የሚገኙ የበረዶ ግግሮች ክብደት ለመለካት ከመሬት በ300 ማይል ርቀት ላይ በመሆን የጨረር ብርሀኑን በደቂቃ 10 ሺ ጊዜ ወደታች በመልቀቅ የመለካት ስራውን ለማከናወን ያግዛል ፡፡

ከጨረሩ በሚያገኘው መረጃ መሰረትም በሚያልፋባቸው ዋልታዎች ላይ መልዕክቶችን ለመላክ ከ1 ቢሊዩን ሰከንድ ባነሰ ግዜ ውስጥም 70 ሲንቲሜትር የሚያህል የመሬት ክፍልን በመለካት ከመሬት ወደ ሳተላይቷ መረጃን ለመላክም ያስችለዋል ፡፡    

በምህዋሮቹ ላይ ሳተላይቱ ለሁለት ሳምንታት ያህል በመዙዋዙዋር አስፈላጊውን መረጃዎች ሁላ ሰብስቦ ይመለሳልም ተብሏል ፡፡

በዚህ ተልእኮ የሰው ልጆች በፕላኔታችን ርቀት ላይ የሚገኙትን ገለልተኛ ክልሎች በማሰስ እና በመሬት ፖሎች የሚካሄደው የበረዶ ሽፋን መለወጥ በመላው ዓለም በህይወት የሚኖሩ ነገሮች ላይ አሁን እና ወደፊት ምን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ  ይህ የጨረር ሳተላይት በእጅጉ ያግዘናል ያሉት የናሳ  የሳይንስ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር  ቶማስ ዘርባቸን  ናቸው ፡፡

ይህ ከፍተኛ የሆነ መረጃን መሰብሰብ የሚችለው ሳተላይት በመሬት ዋልታዎች ላይ የሚገኙ የበረዶ ክምሮች በየግዜው የሚኖራቸውን ለውጥ መረጃን በመሰብሰብ በግሪንላንድና አንታክቲካ ውስጥ የሚገኙ የበረዶ ግግሮች  በመቅለጥ ከባህር ጠለል በላይ ያለቸውን ከፍታ ትክክለኛ መረጃን ለማግኘት ያስችላል ፡፡

ይህም ተመራማሪዎቹ የበረዶውን የመቅለት ሂደት የሚያፋጥኑ ክስተቶችን እና የበረዶዎቹ መቅለጥ በውቂያኖሶችና በአየር ለውጡ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመረዳት ከፍተኛ ሚና አለው ሲል ናሳ አስታውቋል።(ምንጭ: ሜትሮ ኒውስ)

 

 

በሱዳን በደረሰ  የጎርፍ አደረጋ ከአሥር ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል

በሱዳን ከሰኔ ወር አንስቶ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክኒያት የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል፡፡ በደረሰው ጉዳትም 33 መንደሮችና ከአስር ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡

ጎረቤት ሀገር ሱዳን ከሰኔ ወር አንስቶ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ አማካይነት ለጎርፍ መጥለቅለቅ ተዳርጋለች፡፡ ጎርፉ ባሁኑ ሰዓት በደቡብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት እያደረሰ ያለው ጉዳትም ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል ።

በተደጋገሚ በሚጥለው ከባድ ዝናብ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ህይወታቸውን ያጡና አካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥር ያለተገለፀ ቢኆንም በደቡብ ዳርፉር ግዛት አካባቢ ቶኮሊ የተባለችው መንደር ክፉኛ ስለመጎዳቷ የሚድልዲል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

በአካባቢው የጣለው ዝናብ ቁጥራቸው የላቀ ዜጎች ከመንደሩ እንዲሰደዱ ምክንያት መሆኑም ታውቋል ።

በተያያዘም በምስራቅ የሱዳን ግዛት ከ33 በላይ መንደሮች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፤ በአካባቢው የሚገኘው ዳንዳር ወንዝ መሙላቱ የተነሳ ከፍታው 15 ሜትር ከመድረሱ ባለፈ በወንዙ ላይ የሚገኘውን ግድብ ጥሶ ጉዳት አስከትሏል።

አንድ ሺ ቤቶችም በጎርፉ ምክንያት ውድመት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህም በምስራቁ ግዛት ብቻ ከ10 ሺ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ።

ባለፉት ወራት የዓመቱን የዝናብ ወቅት ተከትሎ እየጣለ ያለው ዝናብ በሱዳን በ25 አመታት ውስጥ የከፋው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በመኖሪያ ቤቶች፤ ሆስፒታሎች፤ትምህረት ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ያደረሰው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፤

 

በግብርና ምርትም ከባድ ጉዳት ያደረሰ ሰሆን በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት ሞተዋል፡፡የቱርኩ አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ሰፊ መሬት የሸፈነ የኦቾኖኒ፤ የሰሊጥና የስንዴ ምርት ጉዳት እንደደረሰበት ገልጿል፡፡ በጉዳቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን ቅድሚያ መጠለያ መስጠት አስቸጋሪ መሆኑንም አስነብቧል።

 

በሱዳን ከወር በፊት 48 ሰዎች በጎርፍ ምክኒያት መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን ከ500 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው አይዘነጋም ። በወና ከተማዋ ካርቱም አካባቢ ያለው ሁኔታ እጅግ አሰከፊ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 15 ሺ ቤቶች ወድመዋል፡፡ በጥቅሉ 25 ሺ ቤቶችም እንደ ሀገር ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው ።

 

እየደረሰ ያለውን የጎርፍ ጉዳት ተከትሎ ተላለፊ በሽታ እንዳይዛመት ስጋት ያሳደረ ሲሆን የአለም የጤና ደርጅትም የወባ በሽታ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ እንዲደረግ ገልጿል።