በኢትዮጵያውያን የተሰራችው ሰው አልባ አውሮፕላን 2ኛ የተሳካ የሙከራ በረራ አደረገች

መድኃኒትን ለማጓጓዝ በኢትዮጵያውያን ተነድፋ የተሰራችው ሰው አልባ አውሮፕላን ለ2ኛ ጊዜ የተሳካ የሙከራ በረራ አደረገች፡፡

በረራው በ50 ሜትር ከፍታ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሸፈነ ነው።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሀገራችን ገጠራማ አካባቢዎች እስከ 5 ኪሎግራም የሚደርሱ መድሃኒቶችን በሰው አልባ አውሮፕላን ለማድረስ እየሰሩ ነው፡፡

ከሳምንት በፊት የ25 ሜትር የተሳካ የከፍታ በረራ ሙከራ የተደረገ ሲሆን ትላንት ደብረዘይት አየር ሃይል የተሳካ የበረራ ሙከራ ተደርጓል፡፡

በ5ሺ ሜትር ከፍታ 120 ኪሎሜትር በሰዓት የመብረር አቅም ያላት አውሮፕላኗ ደርሶ መልስ 300 ኪሎሜትር ርዝመት ትበራለች።

በቀጣይ የመጨረሻ ሙከራ ከአዲስ አበባ አዳማ ይደረግና ተጨማሪ 24 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተሰርተው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ምንጭ፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር)