ከ50 ሚሊዮን የሚበልጡ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በመረጃ መረብ ሰርሳሪዎቸ እጅ መግባቱን ፌስቡክ አስታወቀ

በፌስቡክ ላይ በተፈጠረ የግለሰቦች መረጃ ደህንነት አጠባበቅ ከፍተት ሳቢያ ከ50 ሚሊዮን የሚበልጡ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በመረጃ መረብ ሰርሳሪዎቸ እጅ መግባቱን ፌስቡክ አስታወቀ፡፡

ፌስቡክ ላይ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲፈጠር ያሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ ብዙ ተጠቃሚዎችን በማፍራቱ የሚታወቀው ፌስቡክ ይህን የማህበራዊ የትስስር ገጽ ከጓደኞቹ ጋር የፈጠረውና ዛሬ ላይ የፌስብክ ኩባኒያ ዋና ስራ አስፈጻሚም በዓለም ላይ ካሉ ቀደምት አስር ዲታ ቢሊየነሮች ተርታ እንዲሰለፍ የዚሁ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተናኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህ የማህበራዊ ትስስር ገጽ በአሁኑ ሰኣት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ባላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የአፍሪካ አህጉር ህዝብ ሁለት እጥፍ በላይ እንደማለት ነው፡፡ ይህን የተረዱ ኩባኒያዎችም ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን ድንበር ሳይገድበው ለማስተዋወቅ ኩባኒያውን ሁነኛ የማስተወቂያ አውድ አደርገው በመጠቀም በሚሊየን ዶላሮች የሚገመቱ ውሎችን ከኩባኒያው ጋር በመግባት ማስታወቂያ ያስነግራሉ፡፡

ፌስቡክ ኩባኒያም ኢንተርኔት ባለበት ሁሉ ሰዎች ያለምንም ክፍያ የትስስር ገጹን እንዲጠቀሙ  በማድረግ ምርታቸውን እና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁ አካላት በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን እና ደርጅቶች መድርስ እንዲችል አስችሏል፡፡

ይህንን አሰራር በቅጡ የተረዱት የመረጃ መረብ ስርሳሪዎች ደግሞ ለተለያዩ ዓላማዎች የሚፈልጉትን መረጃ መንትፈው ከዚህ ማህበራዊ ትስስር መፍጠሪያ ገጽ ይወስዳሉ፡፡

ከዚህ የተነሳ ፌስቡክም በበርካታ ሰዎች መረጃ ደህንነት ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ከዚህ ቀደም አናሊተካ የተባለ ኩባንያ የአሜሪካን መራጪችን ስነ ልቦና ለመተንተን እና የመራጮችን ሀሳብ ለማስቀየር በማሰብ በሚሊዮን የሚቆረጠሩ ዜጎችን መረጃ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ መውስዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የተጠቃሚዎችን መረጃ ደህንነት ኩባኒያው ማረጋገጥ ባለመቻሉ የኩባኒያው የአክሲዮን ዋጋ ክፉኛ እንዲቀንስ ከማድረጉ በተጨማሪ ኩባኒያው ላይ የህግ ተጠያቂነት ማስከተሉ አይዘነጋም፡፡

አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የመረጃ መረብ መረጃ መንታፊዎች ቪዉ አስን በመጠቀም ከ50 ሚሊየን የሚልቁ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ተጠቃሚዎች አካዉንቶችን መጥለፋቸዉን ኩባንያዉ አስታዉቋል፡፡

የቪው አስ ተግባር የግላዊነት (privacy) አመራጭ ሲሆን የግለሰቡን ዝርዝር መረጃዎች (ፕሮፋይል) ጓደኞቹ የጓደኞቹ ጓደኞች፣ እንዲሁም ሁሉም የፌስቡክ ተጠቃሚ እይታ ውስጥ ያሉ መረጃች ምን ምን እንደሆኑ ለማወቅ እና ለማስተካከል የሚያገዝ አማራጭ እንደሆነም ፌስቡከ አስታዉቋል፡፡

ክፍተቱ ባለፈው ሳምንት መገኘቱን እና ኩባንያዉ የመረጃ መንታፈዎችን  ድርጊት ለፖሊስ አሳዉቆ ከጥቃቱ ጀርባ ያለዉን አካል ለማጣራት ምርመራ እየተካሄድ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ተጠቃሚዎችም አካውንታቸውን ዳግም እንዲያስጀምሩ ወይንም ሪሴት እንዲያደርጉ ኩባኒያው የመከረ ሲሆን 40 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ደግሞ በጥንቃቄ የሚጠየቁትን በመሙላት ሊገለገሉ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ይህ ጉዳይ በጣም ኣሳሳቢ ነዉ ያለዉ ኩባኒያው የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የመረጃ ደህንነት ለማረጋገጥ ከ20 ሺህ በላይ ባለሞያዎች ቀጥሮ እያስራ እዳለ አስታውቋል፡፡ (ምንጭ፡- አልጀዚራ)