ጃፓናውያን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታከለበት መንጽር መሥራታቸው ተገለጸ

ጃፓናውያን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታከለበት መነፅር መሥራታቸውን አስታወቁ ።

በተለያዩ  ምክንያቶች ለሚከሰቱ የአይን በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች   በየጊዜው  የሚሠሩ  ሲሆን  ከእነዚህም ውስጥ ደግሞ የመነፅርና የመድሃኒት አቅርቦቶች ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡

በተለይ በእድሜ መግፋት ምክንያት የሚከሰትን የአይን በሽታ መፍትሄ አድርጎ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታከለበት አጉልቶ የሚያሳይ መነፅር ከወደ ጃፓን ተሰርቷል፡፡

ይሄ ተሰራ የተባለዉ መነፅር ጎኑ ላይ ፎከስ ተች የሚል ቁልፍ የተገጠመለት ሲሆን ይህ ደግሞ ተጠቃሚውን ለይቶ ማየት የፈለገዉን የትኩረት ቦታ አቅርቦ እንዲያይ የሚያስችል ነዉ ተብሏል፡፡

ሲታይ እንደ ማንኛዉም አይነት የፀሃይና የብርሃን መቀነሻ መነፅር የሚመስለው ይህ መነፅር ጎኑ ላይ የተገጠመለትን ሴንሰር ነካ ሲያደርጉ ግን ብልጭ የሚል ነገር በመነፅሩ ብርጭቆ ላይ ይታያል፡፡

በመነፅሩ የተገጠመዉ ሴንሰር በመጫን የመነፅሩ ፍሬም ላይ አነስተኛ አነጸባራቂ ጠቋሚዉ ወደ ፍሬሙ ታችኛዉ ክፍል በመዉረድ ተጠቃሚዉ ሊያየዉ የፈለገዉን ጉዳይ አጉልቶ እና አቅርቦ እንዲያይም ያግዘዋል፡፡

ከዚያም በመቀጠል ሴንሰሩን በመንካት ብቻ ወደ ቀደመ ቦታዉ እንዲመለስ ያደርጋልም ተብሏል፡፡

ባይፎካል ትራይፎካል እና ቫሪፎካል የተሰኙ የመነፅር አይነቶች ተጠቃሚው በአንድ መነፅር አድርጎ ግን ደግሞ ሁለቱም መስታዎቶችን በተለያየ ርቀት እንዲያይ የሚያስችሉ ቢሆኑም ለተጠቃሚ ግን ምቹነት የሌላቸዉ መሆናቸዉን የቢቢሲ መረጃ አመልክቷል፡፡

አሁን ጃፓናዉያን የሰሩት መነፅር ግን በተለይም ደግሞ አሁን ላይ በአለም ላይ አያጋጠመ ላለዉ የእድሜ ላይ የእይታ ችግርን ለመፍታት ጥሩ የፈጠራ ዉጤት እንደሆነ በዘገባዉ ተመላክቷል፡፡