ናሳ የፕላኔት ማርስን ውስጣዊ ይዘት መመርመር የሚያስችል ሮቦት ወደ ማርስ ሊልክ መሆኑን ገለጸ

የአሜሪካው የህዋ ምርምር ተቋም ናሳ የፕላኔት ማርስን ውስጣዊ ይዘት መመርመር የሚያስችል ሮቦት ወደ ማርስ ሊልክ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ወደ ማርስ የምትላከዉ ሮቦት በፕላኔቷ ሰሜናዊ አቅጣጫ ኢሊሲየም ፕላኒሺያ በተሰኘዉ የፕላኔቷ ቦታ እንደሚያርፍም ተገልጿል፡፡

በዋናነት ወደ ማርስ የሚላከዉ ኢንሳይት ላንደር የተሰኘዉ ሮቦት የማርስን አለታማ ዉስጥ ባህሪ ለማጥናት ሲሆን በተለይም የፕላኔቷን ሰሜናዊ ክፍል ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡

ሮቦቱ በአዉሮፓ ሃገራት የተሰሩ የተለያዩ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚያስችሉና በተለይም የፕላኔቷን ዉስጣዊ አለታማ ባህሪ ለማወቅ የሚያግዙ መሳሪያዎችን በዉስጡ ይዞ እንደሚሄድም ነዉ የተገለፀዉ፡፡

ልክ ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረዉ ተልእኮ ኢንሳይት የተሰኘዉ ሮቦት በሰባት ደቂቃ ዉስጥ የማርስን አለታማ መሬት ሰንጥቆ መመርመር ይጠበቅበታል የተባለ ሲሆን ሮቦቱ የማርስን አለታማ መሬት በስቶ በመግባት ጥናቱን ያካሂዳል፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች ወደ ማርስ ለመሄድና ጥናታቸዉን ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ የተናገሩት በናሳ የሳይንስ ክፍል ዋና ስራ አስኪያጅ ቶማስ ዙርበች ከ50 በመቶ ያነሰ ሙከራዎችን እያካሄዱ እንደሚገኙና ወደ ማርስ የሚደረገዉ ጉዞ ከባድ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ኢንሳይት ሮቦት ከዚህ ቀደም ኢንሳይት በዚህ ምርምር ዘርፍ ላይ ጥናት ያደረገ ሲሆን ቀደም ሲል ለጥናት ጥቅም ላይ የዋሉት የቀለጠ የአለት ፣ፓራሹት እና ጠንካራ አለቶች አሁን ሮቦቱ እንዲያርፍ በሚደረግበት ቦታ ግብአት የሚዉል በመሆኑ ማርስ ላይ የሚደረገዉን ጥናት ስኬታማ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡

ወደ ማርስ በሚደረገዉ ጉዞ ሊገጥመን የሚችለዉን ችግር ከግምት ዉስጥ በማስገባት አስፈላጊዉ ዝግጅት መደረጉን ደግሞ የፕሮጀክቱ አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት ቶም ሆፍማን ገልፀዋል፡፡

በካሊፎርኒያ ካምፓስ ምርምር ላብራቶሪ ዉስጥ ይህንን ተልእኮ በመቆጣጠር እየሰሩ ያሉ ኢንጅነሮች የጥናቱ ስኬታማ ዉጤቶችን ይዞ እንደሚመጣ እምነታቸዉ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በፕላኔት ማርስ በኩል ግን ተቀያያሪ የሆነ ጸባይ ሊኖር ስለሚችል ቀድመን ተዘጋጅተናል ሲሉ ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉ መግለፃቸውን  ያስነበበዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡