ቻይናዊያን ሳይንቲስቶች መዳብን ወደ ወርቅ ለመቀየር የተለያዩ ምርምሮች እያደረጉ መሆናቸውን ገለፁ

ቻይናዊያን ሳይንቲስቶች መዳብን ወደ ወርቅ ለመቀየር የተለያዩ ምርምሮች እያደረጉ መሆናቸዉን ገለፁ፡፡  

ቻይና በአለማችን ካሉ ሀገራት ለየት ባለ መልኩ በየጊዜዉ አዳዲስ የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶችን በማስተዋወቅ ላይ  መሆኗ ይታወቃል፡፡ በዚህም ሀገሪቱ  የቴክኖሎጂ መንደር መሆን ችላለች፡፡ 

በሀገሪቱ  የሚገኙ የቴክኖሎጂ ጠበብቶችም ከዚህ ቀደም  በርካታ ሰዎችን የሚያሥደምም ስራዎችን መስራታቸዉ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ደሞ ሳይንቲስቶቿ ከመዳብ ወርቅ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡

ቻይናዉያን  ሳይንቲስቶቹ  መዳብ ላይ ንጥረ ነገር በመጨመር የወርቅና የነሀስ ባህሪ እንዲኖረዉ ለማድረግ ምርምር ላይ መሆናቸዉን የገለጹት ሲሆን በምርምራቸዉም ተስፋ ሰጪ ነገር መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ሳይቲስቶቹ በመዳብ ላይ በመመስረት እያካሄዱት ባለው ምርምር ከሰልን ወደ ፈሳሽነት በመቀየር ዉህደት ይፈጥራል፡፡ ይህም ዋጋቸዉ ዉድ የሆኑ ብረቶች ወይንም ወርቅ እንድናኝ ያስችላል ተብሏል፡፡      

ግኝቱ ተግባራዊ የሚሆነዉ በከሰል ኬሚካል ኢንዳስትሪዎች ላይ መሆኑን በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ዳሊያን ኢንስቲትዩት የጥናት ቡድን መሪ ሰን ጠቁመዋል፡፡

ጥናቱ  ቻይና ያላትን እምቅ የከሰል ሀብቱዋን እንድትጠቀም ከማስቻሉም በላይ ከብክለት የፀዳ የኃይል ምንጭ ለማግኘት ያስችላል፡፡

ሰን እንደሚሉት የጥናት ቡድኑን በመያዝ ንጥረ ነገሩን ተጠቅመዉ ወደ ዉድ ብረትነት ለመቀየር የበለጠ አስቸኳይ ሁኔታዎችን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

የጥናቱ  ግኝት በከሰል ኬሚካል ኢንዳስትሪዉ ሊገደብ እንደማይችል የተናገሩት የጥናት ቡድኑ መሪ በሌሎች አካባቢዎችም ሰፋ ባለ መልኩ ሊተገበር ይችላል ማለታቸዉንም ዘገባዉ አመላክቷል፡፡  

በተካሄደዉ ምርምር  መዳብን በቀጥታ ወደ ወርቅ መቀየር ያስችላል ማለት እንዳልሆነ የተጠቆመ ሲሆን  ነገር ግን  በርከታ ግራም ያላቸዉ አቀጣጣይ ንጥረ ነገሮች በመምረት ላይ ቢሆኑም ወደ ዉጤት የመቀየሩ ሂደት ገና በሙከራ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-ሲጂቲኤን)