ኢንስቲትዩቱ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የባለድርሻ አካላት በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ሥልጠና ሠጠ

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዮት  በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላሉት ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክት ማናጅመንት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከትች ኤንደ ሰርቭ ፎር አፍሪካ (TASFA) እና ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰርቪስ አንስቲትዩት (EDSI) ጋር በመተባበር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላሉት ተቋማት አመራሮችና ውሳኔ ሰጪ አካላት በፕሮጀክት ማናጅመንት ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ትች ኤንደ ሰርቭ ፎር አፍሪካ መቀመጫውን በአሜሪካን ሜሪላንድ ያደረገ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ የበጎ አድራጎት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች የሚሳተፉበት ድርጅት ሲሆን አላማው በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን በተለያዩ ሙያዎች በስልጠና ማብቃት ነው፡፡ 

በፕሮገራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር  ጌታሁን መኩርያ ድርጅቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመስራት ያለው ፍላጎት በዘርፉ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማፋጠን የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)