24 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ኢንተርኔትን እንደሚጠቀሙ ተገለጸ

ከአፍሪካ ህዝብ ውስጥ 24 በመቶ ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸውን ዓለም ባንክ አስታወቀ፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት አለመስፋፋት በአህጉሪቱ አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የስራ ዕድል ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አዳጋች እንደሚሆን ነው ባንኩ የገለጸው፡፡

በአፍሪካ እኤአ ከ2015 እስከ 2035 ባለው ጊዜ ውስጥ 450 ሚሊዮን ስራ ፈላጊ ወጣቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የዓለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ በጥምረት ያወጡት ሪፖርት ያመለክታል፡፡

እንደ ኢኮሜርስ እና ፋይናንስ ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎችን በአፍሪካ በማስፋፋት ከፍተኛ የስራ እድልን መፍጠር እንደሚቻል ተጠቅሷል፡፡

በዚህም፣ ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ ማሰማራት እንደሚገባ ተነግሯል፡፡ (ምንጭ፡-ሲኤንኤን)