የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች የሰሯት አውሮፕላን አፍሪካውያን ቴክኖሎጂን መፍጠር እንደሚችሉ ማሳያ ናት ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ገለጹ፡፡
የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች የሰሯትን አውሮፕላን እያበረሩ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ-ግብፅ ካይሮ አቅንተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ጉዟቸውን እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ “ከዩ ድሪም ግሎባል” መስራች ወጋን ዋርነርና አባላት ጋር በመወያየት ለአባላቱም ሽኝትም አድርገውላቸዋል፡፡
ሙሉ ለሙሉ በደቡብ አፍሪካውያን ታዳጊዎች በተሰራችው በዚህ የአውሮፕን ስራ ውሰጥ 20 ታዳጊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ቴክኖሎጂ ማፍለቅ የቦታ ገደብ የለውም ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ህፃናት እድል ከተሰጣቸው እና ከተደገፉ የማይቻል ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵየውያን ወጣቶችም ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
የዩ ድሪም መስራች ወጋን ዋርነር ይህችን አውሮፕላን ሰርተን በአፍሪካ ሀገራት መዘዋወራችን ምንም ነገር መስራት እንደምንችል ለማሳየት እና ለወጣቶች መነሳሳትን ለመፍጠር ነው ብላለች፡፡ መረጃው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡