ፑቲን በሩሲያ ባህር ሰርጓጅ መርከብ ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን ይፋ አደረጉ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ ባህር ሰርጓጅ መርከብ ላይ ከመርከቧ ኒውክሌር ኃይል ማብላያ በተነሳ እሳት አደጋ መድረሱን ይፋ አደረጉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሰርጓጅ መርከቧ ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን ይፋ ያደረጉት በአደጋው የ14 ባህርተኞች ሕይወት ካለፈ ከሶስት ቀን በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በትናትናው ዕለት አደጋው ከደረሰበት ሰቨሮሞስክ የአርክቲክ ባህርተኞች ሰፈር ደርሰው የተመለሉትን የመከላከያ ሚኒስትሩን ሰርጌ ሾይጉን በሰርጓጅ መርከቧ የኒውክሌር ማብላያ ዙሪያ ማነጋገራቸው ነው የተነገረው፡፡

የመከላከያ ሚኒስተሩ በበኩላቸው የሰርጓጅ መርከቧ የኒውክሌር ማብላያ ችግር መፈታቱንና በስራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የእሳት አደጋው ከመርከቧ ባትሬ ክፍል ላይ መነሳቱን በቴሌቪዥን በተላላፈ መልዕክት አስረድተዋል፡፡

ቀደም ሲልም በዚሁ አደጋ 14 ሰዎች መሞታቸውንና ምን ያህሎቹ እደተረፉ ያለመታወቁን ገልጸው እንደነበረ ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሰርጓጅ መርከቧ በሩሲያ ባረንትስ ባህር ባህር ዳርቻ የውሃ ጥልቀት ልኬት ተልዕኮ ላይ እንደነበረች የተገለጸ ሲሆን÷ ከእሳት አደጋው ጋር የተያያዙ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ያለመውጣተቸውን ዘገባው ያስረዳል  መረጃዉ የአልጀዚራ ነዉ፡፡