የናሳው ሳይንቲስት የሆነው የጠፈር ተመራማሪ አስትሮኖት ዳንኤል ታኒ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለታዳጊ ተማሪዎች በሙያው ያካበተውን ልምድ አጋርቶአቸዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ የሚደረጉ የጥናት እና የምርምር ስራዎቹን ከመቸውም በበለጠ በተጠናከረ ሁኔታ እየሥራ መሆኑን በማንሳት በዘርፉ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎች በሀገሪቱ እዲበራከቱም አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከአስትሮናትስ ዳንኤል ጋር ቆይታ ያደረጉት ተማሪዎቹ ያላቸውን ፍላጎት ይበልጥ የጨመረ እና አስተማሪ ግዜ እንደነበራቸው ለዋልታ ተናግረዋል፡፡
በ1996 ዓ.ም ተመስርቶ እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጲያ ስፔስ ሳይንስስ ሶሳይቲ አጀማመሩ አልጋ በአልጋ አልነበረምአሁን ላይ የህብረተሰቡን አመለካካት ለመቀየር በተሰሩ ስራዎች ልውጦች እየታዩ ሲሆን መንግስትም የጠፈር ሳይንስ ለሀገር ዕድገት ያለውን ሚና በመረዳት የእድገት ግቦቹን አስተሳስሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ሶሳይቲው ከኢትዩጵያ ፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት እና ከአሜሪካን ኤንባሲ ጋር በመተባበር የግዙፉ የጠፈር ሳይንስ ጣቢያ በሆነው ናሳ ውስጥ አስትሮናትስ በመሆን ለ16 አመታት የሰራውን ዳንኤል ታኒ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ በማምጣት በዘርፉ ያለውን ልምድ ለታዳጊዎች አጋርቷል ፡፡
የኢትዮጲያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ በአሜሪካ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የጠፈር ሳይንስ አንቀሳቃሺ ተቋም የሆነው ናሳ ሰራተኞች ወደ ሀገራችን መመላለስ ከጀመሩ ትንሽ ሰንበትበት ብለዋል በማለት ዳንኤለም ወደ ህዋ ሲመላለሱ የኞሩ ሳይንቲስትና ምሀንዲስ ናቸው ታዲያ እኒህ ሰው ወደዚህ መተው ያስተላለፉት መልዕክት ልዕኔ ትልዕቁ ስኬት ነው ብለዋል፡፡
አለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ መግባት መቻላቸው ለትልልቅ አመለካከቶች እና አውቀቶች መማር እና ክህሎቶችን ለመገንባት እድል ሰጥቶናልም ነው ያሉት፡፡
በጠፈር ሳይንስ ላይ የሚሰራ ትልቅ ባለሙያን በአካል አግኝተው ያደረጉት ቆይታ በውስጣቸው ያለውን አስትሮኖት የመሆን ፍላጎትን አውን ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ያነጋገርናቸው ታዳጊዎች ገልጸዋል፡፡